ሳዑዲ ተጨማሪ አምስት ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች።ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደንዛዥ ዕጽ በድብቅ ሲያስገቡ ተይዘዋል የተባሉት ኢትዮጵ…

- Advertisement -
Sidebar AD

ሳዑዲ ተጨማሪ አምስት ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች።
ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደንዛዥ ዕጽ በድብቅ ሲያስገቡ ተይዘዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያን በሞት የተቀጡት ሰኞ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም. በአሲር ግዛት መሆኑን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሳዑዲ መንግስት የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር 17 ደርሷል። ሰኔ 16 አምስት፣ ሰኔ 1 አራት፣ ሚያዚያ 13/2018 ዓ/ም ሦስት ኢትዮጵያውያን በሞት ተቀጥተዋል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው፣ “የፀጥታ አካላት ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር አውለው ባደረጉት ምርመራ ጥፋቱን መፈጸማቸው በመረጋገጡ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተደርጓል” ብሏል።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ቢጠየቅም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ብይኑን በማጽናቱ እና በሸሪዓ ሕግ መሠረት የንጉሣዊ ትዕዛዙ ተፈጻሚ አንዲሆን መደረጉ ተገልጿል።
የሞት ቅጣቱ ዓላማ “የዜጎችን ደኅንነት ለመከላከል እና ነዋሪዎችን ከአደንዛዥ ዕፅ አደጋ ለመጠበቅ እንዲሁም አደንዛዥ ዕፅን ለሚያዘዋውሩ እና ለሚያስፋፉ አካላት በሕግ የተደነገጉትን እጅግ ከባድ ቅጣቶች ተፈጸሚ ማድረግ” መሆኑን ተጠቅሷል። #Bbc
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2