#Ethiopia | የኮሎምቢያ ተመራጭ ፕሬዚዳንት አበላርዶ ደላ ኤስፕሪዬላ በመንግሥት ወጪ ቅነሳ እና በውጭ ፖሊሲ ማሻሻያ ምክንያት በኢትዮጵያ የሚገኘውን ኤምባሲያቸውን ለመዝጋት ማቀዳቸው ተገለጸ።
በፊታችን ነሐሴ 1 ቀን ሥልጣናቸውን የሚረከቡት አዲሱ ፕሬዚዳንት በመጀመሪያው ዙር የዲፕሎማሲ መዋቅር ለውጥ ኢትዮጵያን፣ ደቡብ አፍሪካን፣ ጋናን እና ሴኔጋልን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 14 ኤምባሲዎችን እና ወደ 15 የሚጠጉ ቆንስላዎችን የመዝጋት ዕቅድ አላቸው።
ይህ እርምጃ ሀገሪቱ በአፍሪካ አህጉር ያላትን የዲፕሎማሲ ተሳትፎ በእጅጉ የሚያጠበው ነው ተብሏል።
ኤምባሲዎቻቸው በሚዘጋባቸው ሀገራት የሚኖሩ የኮሎምቢያ ዜጎችም በአቅራቢያቸው ከሚገኙ አጎራባች ሀገራት አገልግሎት የሚያገኙ ይሆናል።
ከዚህ የዲፕሎማሲ ቅነሳ የሚቆጠበው በጀት እንደ ጸጥታ፣ ጤና፣ ትምህርት እና መሠረተ ልማት ባሉ የሀገር ውስጥ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች ላይ እንደሚዋልም ታውቋል።
ከኤምባሲዎች መዘጋት ጎን ለጎን አዲሱ አስተዳደር በውጭ ፖሊሲው ላይ ከፍተኛ የሥራ አቅጣጫ ለውጥ የሚያደርግ ሲሆን ከእስራኤል ጋር የነበረውን ግንኙነት ማደስ ኤምባሲያቸውን ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወር እንዲሁም ከኩባና ኒካራጓ ጋር የነበረውን መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጥን ያካትታል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.