ስለ እርሷ በአደባባይ ክፉ አላወራም

- Advertisement -
Sidebar AD

📌ድምጻዊ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) በሰይፉ ሾው

#Ethiopia | ​ሰይፉ ፋንታሁን፦ከፍቅረኛህን የት አየሃት?

አህመድ ተሾመ፦ የአዲስ አበባ ልጅ ነች፤የአሮጌው ቄራ ልጅ። ያገኘኋት የመን ነው። የእናቴ ሀገር እዚያ በመሆኑ አያቴም በዛ ነበረች። እንዲያውም ከእኛ ቤተሰብ ውስጥ አያታችንን ያየ ብቸኛው ልጅ እኔ ነኝ፤ እዚያው ነው የተዋወቅ ነው።አያቴንም አግኝታታለች።

​ሰይፉ ፋንታሁን፦ ግንኙነታችሁ እስከ “ያማል” ደረጃ ደርሶ እንኔድትለያዩ ያደረጋችሁ ምንድን ነው?

አህመድ ፦ ነገሮች በህይወት ውስጥ ባልሰብነው መንገድ ሊከሰቱ ይችላሉ። ህይወት ሁልጊዜ አንተ በፈለግከውና በታቀድከው አቅጣጫ ብቻ አትሄድም፤ አላህ በፈቀደው መንገድ ነው የምትጓዘው። እኔ ፍጹም ነኝ እያልኩ አይደለም፤ ነገር ግን ለእዚያ ፍቅር ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍያለሁ።

​ሰይፉ ፦ አብራችሁ ምን ያህል ጊዜ አሳለፋችሁ?

አህመድ ፦ በጣም ረጅም ጊዜ አሳልፈናል። ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው በ1999 ዓ.ም ነው። ከዚያ በኋላ ስምንት ዓመት አብረን ቆየን፤ በመሃል አራት ዓመት ተለያየን፤ እንደገና ተመልሰን አንድ ዓመት አብረን ከቆየን በኋላ በመጨረሻ ተለያየን።

​ሰይፉ ፦ እንግዲህ በሃትሪክ (ሦስተኛው) ላይ ደግሞ አትለያዩማ?

አህመድ ፦ አይ፣ ሃትሪኩ ሳይደርስ እኮ “ይረፍዳል” የሚለውን ሥራ ሰራሁ! በአልበሜ ላይ “ያማል”፣ “ይረፍዳል” እና “አይበለው” የሚሉ ዘፈኖች አሉኝ። እነዚህ ዘፈኖች ከህይወቴ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ናቸው።

አልበሜን በጥቅሉ የሰማ ሰው ማንነቴንና ያለፍኩበትን ህይወት በግልጽ ያያል።

​ሰይፉ ፦ አሁን ባለው ሁኔታ ለአዲስ የፍቅር ህይወት ራስህን አዘጋጅተሃል ወይንስ የልብህን በር ዘግተሃል?

አህመድ ፦ ለጊዜው ትኩረቴ በስራዬ ላይ ነው፤ ጥሩ ጥሩ ስራዎችን ሰርቼ ማቅረብ እፈልጋለሁ።

ነገር ግን የህይወቴን በር ሙሉ በሙሉ አልዘጋሁም። ማንም ሰው ቢሆን ተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ መኖር ይፈልጋል። አላህ ደግሞ ያንን ያደርግልኛል ብዬ እመኛለሁ። በህይወቴ የተቆጨሁበት ነገር የለም፤ ሁሉም በራሱ ጊዜ የሚሆን ነው።

​ሰይፉ ፦ ስለነበረው የፍቅር ህይወትህ አሁን ላይ ሆነህ ስታስበው ምን ይሰማሃል?

አህመድ ፦ መጀመሪያ አካባቢ ከተፈጠረው ነገር አንጻር ደስ የማይል ስሜት ነበረኝ። ነገር ግን እኔ የሰውን ገበና ወጥቼ መዘርገፍ አልፈልግም። ያሳለፍከውን ህይወት በአደባባይ ማውጣት ተገቢ አይደለም፤ በጣም ነው የምቃወመው። እሷ በጣም ጥሩ ሰው ነበረች፤ ነገር ግን አልተሳካም።እንኳንስ ካፈቀርካ ሴት አንድ ቀን አብረህ ከበላህ ሰው ክፉ አይወራም ደግ ደግ ነው ሚያዝ ።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: