በምስራቅ አርሲ ዞን በታጣቂዎች የተፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ይፋ ሆኑ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በታጣቂ ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች ላይ ያከናወነውን የምርመራ ግኝት የያዘ 158ኛ ልዩ መግለጫውን ይፋ አድርጓል። በዞኑ በሚገኙ ሽርካ፣ ሮቤ፣ ጀጁ፣ መርቲ፣ ጉና፣ ሆንቆሎ ዋቤ፣ አርሲ ሲሬ፣ ሙኒሳ እና አሰኮ ወረዳዎች በተፈጸሙት ጥቃቶች በሃይማኖትና ማንነት ላይ ያነጣጠሩ የሰዎች ግ ድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት መከሰታቸው ተረጋገጧል።

​ኢሰመጉ ከመጋቢት 3 እስከ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው የመስክ ምርመራና ከሟች ቤተሰቦች፣ ተጎጂዎች፣ የዓይን እማኞች እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ቤተክህነት ጽሕፈት ቤቶች ባሰበሰባቸው መረጃዎች መሰረት በጥቃቱ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ዓ.ም የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የምርመራ ስራን አከናውኗል፡፡ በተሰበሰበው መረጃ መሰረት:-
📌 በሽርካ ወረዳ 116፣
📌 በመርቲ ወረዳ 117፣
📌 በጀጁ ወረዳ 101፣
📌 በሮቤ ወረዳ 47፣
📌 በጉና ወረዳ 26፣
📌 በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 20፣
📌 በሙኒሳ ወረዳ 19፣
📌 በአሰኮ ወረዳ 5 ንጹሃን እና 4 የጸጥታ አካላት (ሚሊሻዎች) እንዲሁም
📌 በሲሬ ወረዳ 3 ሰዎች ተገ ድለዋል።

​ከግድ ያው በተጨማሪ ከፍተኛ የእገታ ወንጀል የተፈጸመ ሲሆን፣
📍በሮቤ ወረዳ 156 ሰዎች፣
📍በጀጁ ወረዳ 182 ሰዎች፣
📍በመርቲ ወረዳ 29 ሰዎች
📍በሽርካ ወረዳ 39 ሰዎች ታግተው በርካቶቹ በካሳ ክፍያ የተለቀቁ ቢሆንም የበርካታ ታጋቾች የደረሱበት ሁኔታ እስከ አሁን አይታወቅም። እንዲሁም በሕፃናትና አዛውንቶች ላይ የቆሰሉና አካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የአሰኮ ወረዳ የጠለታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ጨምሮ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት መዘረፋቸውና መቃጠላቸው፣ የመኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸው እና የቀንድና የጋማ ከብቶች መዘረፋቸው በምርመራው ተረጋግጧል።

​ኢሰመጉ መንግስት የዜጎችን በሕይወት የመኖርና የንብረት ጥበቃ የማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ፣ በጥሰቱ የተሳተፉ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ እና ለተፈናቀሉት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1