“በስዊድን የጠፉት ታዳጊዎች ብሔራዊ ቡድንን አይወክሉም”

- Advertisement -
Sidebar AD

— የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

#Ethiopia | ​በዓመታዊው የጎቲያ ካፕ ውድድር ላይ ለመካፈል ወደ ስዊድን ያመሩ ታዳጊዎች እና የቡድን አባላት በዚያው መጥፋታቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማብራሪያ ሰጥቷል።

ፌዴሬሽኑ በቡድኑ አባላት መጥፋት እንደሰማ የገለጸ ሲሆን በተለያዩ አካላት ታዳጊዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተወካዮች እንደሆኑ ተደርጎ የሚሰራጨው ዘገባም ሙሉ በሙሉ ትክክል እንዳልሆነ አስታውቋል።

አክሎም መሰል ታዳጊ ቡድኖች ወደ እንዲህ ባሉ ዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያመሩት በራሳቸው ጥረት በሚያገኙት እድል እንጂ አገራቸውን ወክለው በፌዴሬሽኑ አደራጅነት እንዳልሆነ በመግለጽ ጉዳዩን አብራርቷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2