🙏
ቅዱስ ዑራኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏
የስሙን ትርጓሜ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲያስቀምጡም “ዑራ” ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን “ኤል” አምላክ ማለት ነው፡፡
በዚህም ዑራኤል ማለት የአምላክ ብርሃን፣ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው ይላሉ፡፡ መልአከ ብርሃናት፣ ለሚጠሩት ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት በስፋት ይገልጹታል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ይከበራል፡፡
ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ዑራኤል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር በመባርቅትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመው ታላቅ መልአክም ነው ቅዱስ ዑራኤል፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6÷2 መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ይሰማራል። ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለትም የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለነቢዩ ሄኖክ ነግሮታል።
እውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ትእዛዝ ፅዋዐ ጥበብን አጠጥቶ ሠማያዊውን ጥበብ የገለጸለት ቅዱስ ዑራኤል ነው። “ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ” ይላልና፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናብ በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምህረትን የሚለምን ነው ቅዱስ ዑራኤል። ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ግልጽ ነው። በዕዝራ ሱቱኤል 13÷38 ተጽፎ እንደምናገኘው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” ብሎ አእምሮ ለብዎውን ወይም ማስተዋልን ገልጦለታል።
የተወደደ ሥራ ለሚሠሩና እንዲያውቁ ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል፤ ለዕዝራ ሱቱዔል የሆነለትም እንዲሁ ነውና። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፣ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ እርሱ ነው፡፡ ሊቀ መልአኩ የጌታችንን ደም የረጨበት ጽዋ በሀገራችን በኢትዮጵያ እመጓ ቅዱስ ኡራኤል እንደሚገኝ ስፍረዋን የጎበኙ ጸሐፍትና የስፍራው አገልጋዮች ይገልጻሉ፡፡ በርካታ ቅዱሳን አባቶች ምስጢር እንዲገለጥላቸው የረዳቸው ቅዱስ ዑራኤል መሆኑ በበርካታ የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ሰፍሮ ይገኛል፡፡ አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል እንዲናገሩ፣ የሚጽፉበት ብዕር በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ለሕይወት ድህነት የሚሆን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ቅዱስ ዑራኤል አግዟቸዋል፡፡
ይህም ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ያሳየናል፡፡ ዛሬም በየገዳማቱ ያሉ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ዓለምን ንቀው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፤ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ተቋቁመው በጾምና በጸሎት ሲተጉ ይህ ቅዱስ መልአክ ዑራኤል ፈጽሞ ይራዳቸዋል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ 8÷4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።” እንዲል ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደህንነት እግዚአብሔርን በሚለምኑት በገዳማውያኑ መካከል ተገኝቶ ጸሎታቸውን ያሳርጋል፤ ልመናቸውን በአምላክ ፊት ያቀርባል፡፡ ቅዱሳን መካናትን ስናግዝ፣ ገዳማትን ስንረዳ፣ በዓታቸውን ስናጸና የገዳማውያኑ ጸሎትና በረከት ይደርሰናል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Source: Yeneta Tube









No comments yet.