የሰው ልጅ ከ5 እስከ 7 ዓመታት ውስጥ ማርስ ላይ ሊያርፍ እንደሚችል ኢሎን ማስክ ገለጹ
ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ የሰው ልጅ በሚቀጥሉት ከ5 እስከ 7 ዓመታት ውስጥ በማርስ ላይ እግሩን ሊያኖረው እንደሚችል አስታወቁ።
ማስክ ይህንን ያሉት አራት አባላት ያሉት የጠፈር ተመራማሪዎች ቡድን ወደ ማርስ ለመላክ ከ10 እስከ 15 ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል የተናገሩትን የናሳ (NASA) አስተዳዳሪ ጃሬድ አይዛክማን አስተያየት በመቃወም እና ምላሽ በመስጠት ነው።
እንደ ማስክ ማብራሪያ ከሆነ፣ የሰው ልጅን ማርስ ላይ የሚያሳርፈው መንኮራኩር ከተገመተው ጊዜ ይበልጥ ቀደም ብሎ ዝግጁ ሊሆን ይችላል።
የስፔስ ኤክስ ባለቤት የሆኑት ማስክ በማርስ ላይ የሰው ልጅ መኖሪያ ለመገንባት የሚያስችሉ ዘመናዊ የጠፈር መንኮራኩሮችን የማልማት ሥራቸውን አፋጥነው እያከናወኑ ይገኛሉ።
ይህ አዲስ የጊዜ ሰሌዳ በጠፈር ምርምር ዘርፍ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ ሲሆን፣ ወደ ማርስ የሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ ከተጠበቀው በላይ በፍጥነት ሊሳካ እንደሚችል ያመላክታል።
@Seledadotio

No comments yet.