የእዝ እና የድርጅት አመራር የነበሩ 14 አባላት በሐገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ እንደሆነ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተናገሩ

- Advertisement -
Sidebar AD

የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ የተቀላቀሉት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ የዕዝና የድርጅት አመራር የነበሩ 14 አባላት በውክልና ኮታ በሐገራዊ ምክክር መድረኩ እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸዋል።

ካፒቴን ማስረሻ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደገለጹት፣ ታጣቂዎችን ወደ ጫካ ያስገቡት መሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች አሁን ላይ በሃገራዊ ምክክር ጉባኤው እየተመከረባቸው ነው።

አመራሮቹ በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚነሱ ለትጥቅ ትግል መነሻ የሆኑ ጥያቄዎች ለውይይት መቅረባቸውንም አንስተዋል።

“ከጫካ ትግል ተመልሰን፤ ጥያቄዎቻችንን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በጋራ ለመፍታት ለምክክር ተቀምጠናል” ያሉት ካፒቴን ማስረሻ፣ አንገብጋቢ የሚሏቸውን ጉዳዮች በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን አስታውሰዋል።

አሁን ላይ በምክክር መድረኩ እየተመከረባቸው ያሉት 8 አጀንዳዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸው፣ የሀገር ግንባታ እና የመንግስት አወቃቀርን የተመለከቱ ጉዳዮች እልባት የሚፈልጋቸው አንኳር ጥያቄዎች ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ካፒቴን ማስረሻ የምክክር መድረኩ ለዘመናት ሲንከባለሉ ለመጡ ፖለቲካዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ በማምጣት የተሻለ መንገድ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

#አሐዱ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2