የኩርሙክ ወርቅ ማዕድን ሥራውን በነሐሴ ወር ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

👉የቻይናው ግዙፍ ወርቅ አምራች 9 በመቶ ድርሻ ለመውሰድ ተስማምቷል

የካናዳው ማዕድን አምራች ኩባንያ የሆነው አላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የሚገኘውን ግዙፉን የኩርሙክ ወርቅ ማዕድን ማውጫ ፕሮጀክት ግንባታ አጠናቆ በመጪው የነሐሴ ወር ውስጥ ሥራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። ማዕድን ማውጫው ሥራውን ሲጀምር የመጀመሪያውን ወርቅ ምርት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለገበያ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ወሳኝ መረጃ ይፋ የሆነው ከአላይድ ጎልድ እና ከቻይናው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል ጋር የነበረው የ4 ቢሊዮን ዶላር የመገዛት ስምምነት መሰረዙን ተከትሎ ነው።

እንደሚታወሰው የቻይናው ኩባንያ አላይድ ጎልድን በአክሲዮን ለመግዛት አቅዶ አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች በመዘግየታቸው የስምምነቱ የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ሊከበር እንዳልቻለ አላይድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ሆኖም ሁለቱ ኩባንያዎች ሙሉ ግዢውን በመሰረዝ ፋንታ በግንኙነታቸው ለመቀጠል እና አዲስ አጋርነት ለመፍጠር በመስማማታቸው ዚጂን ጎልድ በግምት 295 ሚሊዮን ዶላር ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት በአላይድ ጎልድ ላይ አድርጓል።

በዚህ አዲስ የኢንቨስትመንት ስምምነት መሠረት ዚጂን ጎልድ 12.8 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖችን የሚገዛ ሲሆን፣ ይህም የኩባንያውን 9.2 በመቶ ድርሻ እንዲይዝ ያስችለዋል።

አላይድ ጎልድ እንዳስታወቀው ከዚህ አጋርነት ከሚገኘው የገንዘብ መጠን ውስጥ ከፍተኛው ድርሻ ለኩባንያው ዕድገት ስትራቴጂ፣ ለአሰራር ማሻሻያ እና በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኘውን የኩርሙክ ወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ግንባታ ወደ ምርት ለማሸጋገር ይውላል። ከዚህ በተጨማሪ በ ማሊ የሚገኘውን የሳዲዮላ ማዕድን ማስፋፊያ፣ በኮትዲዕፍዋር ያሉ የምርት ማሳደግ ሥራዎችን እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚደረጉ የፍለጋ ሥራዎችን ፋይናንስ ለማድረግ ያገለግላል ብሏል።

የኩርሙክ ወርቅ ማዕድን ማውጫ ሥራውን መጀመር ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ ያለው ሲሆን፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከማሳደግ ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ በርካታ የስራ እድሎችን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

#ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia #alliedgoldcorp #Mali #cotedivoire #canada #china #ZijinGold Ministry of Finance – Ethiopia Ministry of Mines – Ethiopia Abiy Ahmed Ali


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: