የቀድሞው የኡጋንዳ አምባገነን መሪ ኢዲ አሚን የልጅ ልጅ የስኮትላንድ ንጉሥ ለመሆን እየሰራ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የቀድሞው የኡጋንዳ አምባገነን መሪ ኢዲ አሚን የልጅ ልጅ የሆነው የ25 ዓመቱ አዚዝ አብዱል በግላስጎው እየተካሄደ በሚገኘው የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች በሱፐር ሄቪዌይት ቦክስ ውድድር የሀገሩን ስም ለማስጠራት እየተፋለመ ይገኛል።

​ኢዲ አሚን ስድስት ጊዜ ያገባ ሲሆን በይፋ አምኖ የተቀበላቸውን ጨምሮ ወደ 60 የሚጠጉ ልጆችን ወልዷል። አዚዝ አብዱልም ከእነዚህ በርካታ የዘር ሐረጎች መካከል አንዱ ነው።

“ሪንጎ” በሚለው የቅጽል ስሙ የሚታወቀው አዚዝ ከ90 ኪሎግራም በላይ የክብደት ክፍል ሩብ ፍጻሜ ውድድር እንግሊዛዊውን ዳማር ቶማስን ማሸነፍ ከቻለ የነሐስ ሜዳሊያ ማገኘቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን ይህም ከእ.ኤ.አ 1990 ወዲህ ለኡጋንዳ የመጀመሪያውን የኮመንዌልዝ የቦክስ ሜዳሊያ የሚያስገኝላት ይሆናል።

​ይህ አጋጣሚ በግላስጎው መከሰቱ ለውድድሩ ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል ምክንያቱም አያቱ ኢዲ አሚን በሕይወት በነበሩበት ወቅት ለስኮትላንድ ልዩ ፍቅር የነበራቸው ሲሆን በ1976 እራሳቸውን “የስኮትላንድ ንጉሥ” ብለው እስከመሰየም ደርሰው ነበር።

​አዚዝም ልክ እንደ አያቱ ” ምናልባት አዲሱ የስኮትላንድ ንጉሥ እኔ እሆን ይሆናል ፤ እዚህ እንደደረስኩ ሰንደቅ ዓላማውን ሰቅያለሁ፤ ምክንያቱም ስኮትላንድን እጅግ በጣም እወዳታለሁ። ሀገሬ እንድታውቀኝና እውቅና እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ።” ብሏል

እራሳቸው ኢዲ አሚንም በወጣትነታቸው የኡጋንዳ የላይት ሄቪዌይት ቦክስ ሻምፒዮን እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን የልጅ ልጃቸው አዚዝ ግን የአያቱን አምባገነናዊና አወዛጋቢ ታሪክ ወደ ጎን በማለት በራሱ ስፖርታዊ ስኬት አዲስ ታሪክ ለመጻፍና እየሰራ ይገኛል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1