*በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተማረ የሰው ሀይል በመያዝ ካናዳ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች።
#Ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤታማነት ያላቸውን የትምህርት ሥርዓቶች አስመልክቶ የወጡ ጥናቶች የካናዳ የትምህርት ስርአት ተመራጭ ሆኗል።
በካናዳ ከ25 እስከ 64 የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎች መካከል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው ተብሏል።
ይህም ሀገሪቷን በአለም አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት ተዳራሽነት በማረጋገጥ ከአለም ቀዳሚ አድርጓታል።
ጃፓን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ደቡብ ኮርያ እስራኤል እና አሜሪካ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
ጥብቅ የጥናት ባህልና እጅግ ጥብቅ የሆነው የሀገሪቷ የፈተና ሥርዓቷ ለዚህ ስኬት አብቅቷታል።
ተማሪዎች ለተጨማሪ አጋዥ ትምህርቶችና ለብሔራዊ ፈተናዎች የሚሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ለስኬታቸው እንደ ዋና ምክንያት ተቆጥሯል።
በተጨማሪም የትምህርት ስርአቷ ለመምህራን ከፍተኛ ሙያዊ ክብር መስጠት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።
ሆኖም በሰው ቁጥር ሲሰላ እንደ ቻይና እና ህንድ ያሉ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆኑ ሀገራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተማረ ሰው ይገኝባቸዋል።
ነገር ግን ከጠቅላላ የሀገሪቱ ህዝብ ቁጥር አንፃር ሲሰላ ግን ካናዳ ደረጃውን በበላይነት መያዟ ተረጋግጧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Canada #elite #University
Source: GetuTemesgen









No comments yet.