#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአዲስ አበባ ስቴዲየም በመገኘት፣ በአሜሪካ ኦሪገን ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አበረታቷል ።
ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በንግግራቸው አትሌቶቹ የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ ታሪክና ክብር በሚመጥን መልኩ በትጋት፣ በዲሲፕሊንና በከፍተኛ የውድድር መንፈስ በመወዳደር የሀገራቸውን ባንዲራ በክብር እንዲያውለበልቡና በሜዳሊያ የታጀበ ውጤት ይዘው እንዲመለሱ የሚቻላቸውን እንዲያደርጉ ጠይቋል ።
በተጨማሪም አትሌቶቹ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ቀጣይ ተስፋ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ይህንን እድል በአግባቡ በመጠቀም በዓለም መድረክ አቅማቸውን እንዲያሳዩ አበረታተዋል።
በመጨረሻም ፌዴሬሽኑ ለልዑክ ቡድኑ አስፈላጊውን ድጋፍ በሙሉ እንደሚያደርግ በማረጋገጥ፣ ለአትሌቶቹ፣ ለአሰልጣኞቻቸውና ለመላው የልዑክ ቡድን መልካም እድል ተመኝተዋል።

Source: GetuTemesgen









No comments yet.