የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የCGIAR የመጀመሪያው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ በዓለም አቀፍ የግብርና ምርምር ትብብር ተቋም CGIAR አዲስ የተዋቀረው የቦርድ የመጀመሪያ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸውን ተቋሙ በይፋ አስታውቋል። ሹመታቸው ከነሐሴ 1 ቀን 2026 ጀምሮ በይፋ ተግባራዊ ይሆናል።

እንደ CGIAR መግለጫ፣ አዲሱ ቦርድ የተቋሙን የዓለም አቀፍ የግብርና ምርምር ሥራዎች በማስተባበር በምግብ ዋስትና፣ በግብርና ምርታማነት፣ በአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ የሚከናወኑ ስትራቴጂያዊ ውሳኔዎችን ይመራል።

ሹመቱ የተካሄደው ለወራት የዘለቀ የምልመላና የእጩ ምርጫ ሂደት ተጠናቆ ሲሆን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ በግብርና ፖሊሲ፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ትብብር፣ እንዲሁም በሳይንስን መሠረት ባደረገ የልማት አመራር ያላቸው ልምድ ለሹመታቸው ዋና ምክንያት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

የCGIAR ጊዜያዊ የቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሮኤል መርክስ በሰጡት መግለጫ፣ ኃይለማርያም በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የግብርና ልማትን ለማራመድ ያላቸው ልምድና አመራር ለተቋሙ ትልቅ እሴት እንደሚያመጣ ገልጸዋል።

ኃይለማርያም ደሳለኝ ከ2019 ጀምሮ የAGRA (Alliance for a Green Revolution in Africa) ቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ በተጨማሪም የTradeMark Africa ቦርድን ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የአመራር ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: