#Ethiopia | የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ፣ ባህልና ታሪክ ዘርፍ ከፍ ለማድረግ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ መዋቅራዊና የክህሎት ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ አዲስ አጋርነት ተፈጠረ።
በዚህም መሠረት የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና አባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ይፋዊ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የድርጅቱን የዘመናት ታሪክና የልምድ ክምችት ከአካዳሚው ዘመናዊና ፈጠራ የታከለበት የአሰልጠና ዘዴ ጋር በማጣመር በቴአትር፣ በሙዚቃ፣ በፊልም እና በተዛማጅ የጥበብ ዘርፎች ሰፊ ሥልጠናዎችን ለመስጠት ያለመ ነው።
አዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ብሔራዊ ቴአትርን፣ ሀገርፍቅር ቴአትርን፣ ባህል አዳራሽን፣ ራስ ቴአትርን እና የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትርን የሚያስተዳድር ተቋም እንደ መሆኑ መጠን፣ ይህ አጋርነት አባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ እስካሁን ሲፈትኑት የነበረውን የመድረክ፣ የቦታ እና የሎኬሽን ችግር በዘላቂነት የሚቀርፍ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ወጣትና ህጻናት ተማሪዎችን በማብቃት በልጆች አክቲንግ ዘርፍ አበረታች አስተዋጽኦ ያበረከተው አባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሌንጮ ፍቅሩ፣ ስምምነቱ የሰለጠኑ አዳዲስ ከዋክብትን ወደ ታሪካዊ የቴአትር መድረኮች በቀጥታ ለማውጣት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ሁለቱ ተቋማት የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ወግ የሚያንፀባርቁ ትላልቅ ፕሮዳክሽኖችን፣ ከግጥም ምሽቶች እስከ ታላላቅ የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሎች ያሉ ሁነቶችን በጋራ በማዘጋጀት ለሕዝብ ለማቅረብም ተስማምተዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ /መስፍን
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#EthiopianArt #EthiopianTheatre
#AddisAbaba #ArtCollaboration #CreativeArts #CulturalHeritage #AbaletaActingAcademy



Source: GetuTemesgen









No comments yet.