ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ካርቱም ናቸው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኢጋድ በካርቱም የሚገኘውን ጽ/ቤቱን በድጋሚ ከፈተ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በካርቱም የሚገኘውን ጽህፈት ቤቱን በይፋ በመክፈት ስራ ጀምሯል።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንደገለጹት ቢሮው የሰላም ጥረቶችን ከመደገፍ ባሻገር በካርቱም እና በሌሎች አካባቢዎች የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ለማገዝ እና ከአካባቢው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት ለመነጋገር ነው ብለዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳን የሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፋታህ አል ቡርሃን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ካሜል ኢድሪስ ጋር በሰላም እና በመልሶ ግንባታ ዙርያ ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን አድርገዋል ሲል አናዱሉ የገለፀው።

ኢጋድ በሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Khartoum
#IGAD


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1