ከጋብቻ ውጭ የወለደችውን ልጅ በወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣችበቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ውስጥ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከጋብቻ ውጭ የወለደችውን ልጅ በወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ውስጥ ከጋብቻ ውጭ በጤና ተቋም በሰላም የተገላገለችውን ልጅ  ወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጥታለች።
የጮራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር በለጠ ጉታ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ተከሳሽ ሙሚሻ ሱልጣን የአስራ ዘጠኝ አመት ታዳጊ ወጣት መሆኗን ገልጸዋል።
ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ በሰላም ከጤና ጣቢያ ልጇን ተገላግላ ወደ ቤት ስትገባ ወላጆቿ  ከጋብቻ ውጭ በመውለዷ ባደረሱባት ቁጣ ተፅዕኖ ስር ወድቃ በነጋታው አስር ሰዓት ላይ የወለደችውን ጨቅላ ወንድ ልጅ አፍና ገድላዋለች።  አስክሬኑን ካርቶን ውስጥ ሸሽጋ በማቆየት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ማንም ሳያያት ልትቀብር ስትል በአካባቢው ማህረሰብ ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።
የአራስ ልጇን አስክሬን ወደ ደልቢ ጤና ጣቢያ በመላክ ተከሳሿ ላይ አስፈላጊውን የምርመራ መዝገብ በሰውና በሕክምና ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ተላልፏል። አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን መዝገብ ተመልክቶ በህፃን መግደል ወንጀል ክስ መስርቶባታል።
በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ አስባ የፈፀመችው የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በአስራ አምስት አመት እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን ኢንስፔክተር በለጠ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: