#Ethiopia | ለበርካታ ዓመታት ያለ ህግና ስርዓት ሲመራ የቆየው የኢትዮጵያ የሪል እስቴት ሴክተር፣ በቅርብ ቀናት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ አዋጅና ደንብ ዘርፉን ከህገ-ወጥነት ይታደገዋል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል።
በዑራኤል አደባባይ አካባቢ አዲስ የህንፃ ፕሮጀክት ያስጀመረው ጄጄ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጀበል ጀማል እንደገለጹት፣ አዲሱ አዋጅ የገዢዎችን ገንዘብ አላግባብ ወስዶ የመጥፋት ህገ-ወጥ ድርጊቶችን መቶ በመቶ የሚያስቀር ጠንካራ ማዕቀፍ የያዘ ነው።
በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከአሁን በኋላ የሚሰበሰበው የቤት ገዢዎች ገንዘብ በዝግ አካውንት ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ስራው በእንቅስቃሴ ልክ መድረሱን አረጋግጦ በመንግስት አካላት ሲረጋገጥ ብቻ ለባንክ የሚለቀቅበት ስርአት እንደሚዘረጋ ተመላክቷል።
ይህ አሰራር ገንዘብ ተወስዶ ቤት ሳይገነባ የሚቀርበትን እድል ሙሉ በሙሉ በማስቀረት የገዢዎችንና የአልሚዎችን ደህንነት በአንድ ላይ እንደሚያስጠብቅ ተገልጿል።
በዚህ አዲስ ማዕቀፍ ውስጥ በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ በርካታ ዓመታት ያሳለፈው ጄጄ ግሩፕ በዑራኤል አደባባይ አካባቢ እጅግ ዘመናዊ የሆነ አዲስ የህንፃ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ያስጀመረ ሲሆን፣ ባለ 12 ወለል የሆነው ይህ ዘመናዊ ህንፃ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ 31 አፓርትመንቶች እንዲሁም ከ60 በላይ የተለያዩ ሱቆችን አካትቶ ይይዛል።
ህንፃው ለነዋሪዎች ምቹ እና ጸጥታ የሰፈነበት እንዲሆን ከንግድ ስራው ጋር በቀጥታ እንዳይገናኝ ተደርጎ በጥንቃቄ የተነደፈ መሆኑን አቶ ጀበል ጀማል ገልጸዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ኢትዮጵያ #ሪልእቴት #ጄጄግሩፕ #አዲስአበባ #የኮንስትራክሽንዜና #Ethiopia #RealEstate



Source: GetuTemesgen









No comments yet.