ኳታር ከኢንፋንቲኖ ጎን ናት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኳታር እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ “ፊፋ ፎርዋርድ ኢንተርፕራይዝ” የተሰኘውን የውሳኔ ሃሳብ ለማንሳት ያሳለፉትን ውሳኔ በሙሉ ደስታ መቀበሉን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ እንዳመለከተው ይህ እርምጃ የመላው ዓለም እግር ኳስ ቤተሰብን የጋራ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ እና አወንታዊ እርምጃ ነው።

​የኳታር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሼክ ሀማድ ቢን ካሊፋ ቢን አህመድ አልታኒ በሰጡት መግለጫ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ብዙ መልካም ጎኖች የነበሩት ቢሆንም በርካታ ከአባል ሀገራት ፌዴሬሽኖች አልተቀበሉትም ብለዋል።

አክለውም ለአባል ሀገራት አንድነት ቅድሚያ በመስጠት የተወሰደው ይህ ውሳኔ ትልቅ ጥበብ የተሞላበት መሆኑን በመጠቆም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

​በመጨረሻም ፌዴሬሽኑ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የዓለም እግር ኳስን ለማሳደግ እና የበለጠ ለማጠናከር የሚያደርጉትን ማንኛውንም ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍና ከጎናቸው እንደሚቆም አረጋግጧል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1