#Ethiopia | በትላንትናው እለት ከሞሮኮ መነሻቸውን አድርገው ስፔንን አጥለቅልቀው የነበሩት ስደተኞች ወደ መጡበት እየተመለሱ ይገኛል።
ኪዩታ ወደ ተሰኘችው የስፔን ከተማ የገቡት 60,000 የሚጠጉ ስደተኞቹ በዛሬው እለት ወደ ሞሮኮ በፍቃደኝነት እየተመለሱ መሆናቸውን አልጀዚራ ጽፏል።
የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆዜ ማኑኤል አልቫሬዝ እንደገለፁት ሀገራቸው የስደተኞች ነፃነትና መብት እንደምታከብር ገልጸው ህገወጥ መንገድ ግን በየትኛውም መንገድ አንቀበልም ብለዋል።
አሁን በወጡ መረጃዎች መሠረት በህገወጥ መንገድ ከገቡት ስደተኞች መካከል 67 የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል ሲሉም ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት ሀላፊ ኡርሱላ ቮንደርላይን የስደተኞቹ ድርጊት ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረው ሀገራት ድንበራቸውን ጥብቅ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር በበኩላቸው ሀገራቸውን ከስፔን የምትዋሰንበት ድንበር ማጠናከሯን ገልጸዋል።
የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ድንበሮቻቸውን ክፍት አድርገው ስፔንን በስደተኞች እንድትወረር ያደረጉ ሀገራትን ክፍኛ ተችተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Spain #migrants #Ceuta
#EuropeanUnion
#UrsulavonderLeyen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.