ኢትዮጵያዊው የባህልና ኪነ-ጥበብ መሪ አቶ ገብረማርያም ይርጋ ዓለም አቀፍ ሽልማት ተቀበሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኢትዮጵያዊው የባህልና ኪነ-ጥበብ መሪ አቶ ገብረማርያም ይርጋ አለማየሁ በባህል ልማት፣ በባህል ዲፕሎማሲ፣ በፈጠራ አመራር እና በዓለም አቀፍ የባህል ትብብር ግንባታ ላይ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ የ2026 International Cultural Development Professional Award ተሸላሚ ሆነዋል።

ሽልማቱ በታይላንድ በተካሄደው Korat International Folklore Festival (KIFF) የተሰጠ ሲሆን፣ በሰርተፊኬቱ ላይ እንደተገለጸው እውቅናው ለእርሳቸው በልዩ ትጋት፣ በሙያዊ ብቃት፣ በአመራር ብቃት እና በባህል ልማት ዘርፍ ላበረከቱት ፈጠራዊ አስተዋፅኦ መሰጠቱ ተጠቅሷል።

ይህ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የኢትዮጵያን ባህል፣ ኪነ-ጥበብ፣ የአርቲስቶች ፈጠራ እና የሀገሪቱን የባህል ዲፕሎማሲ በዓለም መድረክ እየተጎለበተ መሆኑን የሚያሳይ ክብር መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ገብረማርያም ይርጋ በሰጡት አስተያየት፣ ሽልማቱ ለተሻለ ሥራ የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቅሰው፣ “ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የባህል ባለሙያዎች፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎች እና ባህላችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያሸጋግሩ ለቆዩት ሁሉ የተሰጠ እውቅና ነው” ብለዋል።

እንዲሁም ይህ ክብር ባህልና ኪነ-ጥበብ በሕዝቦች መካከል ወዳጅነትን እና መግባባትን የሚያጠናክር ኃይል እንዳለው የሚያረጋግጥ ታሪካዊ እውቅና መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ የጥንታዊ ሥልጣኔ መገኛ ብቻ ሳትሆን የባህልና ጥበብ መናገሻ ሀገር መሆኗን በተግባር ማሳየቷን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

እንኳን ደስ አለዎት!
ይህ ዓለም አቀፋዊ ክብር ለኢትዮጵያ ባህልና ኪነ-ጥበብ የተገኘ ትልቅ ኩራት ነው።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2