«ግሩፕ 26» የተባለው የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች አባል የሆነ ወታደራዊ ቡድን ለሱዳን ጦር እጁን ሰጠየሱዳን ፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (…

- Advertisement -
Sidebar AD
«ግሩፕ 26» የተባለው የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች አባል የሆነ ወታደራዊ ቡድን ለሱዳን ጦር እጁን ሰጠ
የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) አባል የሆነው እና «ግሩፕ 26» በመባል የሚታወቀው ወታደራዊ ቡድን በኦምዱርማን አካባቢ ለሱዳን ጦር (SAF) እጁን መስጠቱን፣ አባላቱን እና ወታደራዊ ትጥቆቹን ማስረከቡን የሱዳን ዜና ኤጀንሲ (SUNA) ዘገበ።
ወደ 45 የሚጠጉ ተዋጊዎችን እና መኮንኖችን የያዘው ይህ ቡድን፣ የሱዳን ጦር በቅርቡ በሰሜን ኮርዶፋን ያደረገውን ግስገሳ ተከተሎ ከባራ እና ከሌሎች የአካባቢው ስፍራዎች በመሸሽ የመጣ እንደሆነ ተገልጿል። 
ተዋጊዎቹ የውጊያ ተሽከርካሪዎችን እና የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን ጨምሮ ሙሉ ወታደራዊ ትጥቃቸውን ይዘው እጃቸውን መስጠታቸውን ሱና ዘግቧል።
ይህ ክስተት የተፈጸመው የሱዳን ጦር ኤል ኦቤይድን ከዋና ከተማዋ ጋር የሚያገናኙ ስትራቴጂካዊ መስመሮችን ጨምሮ በሰሜን ኮርዶፋን ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ባሰፋበት ወቅት ነው።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1