ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት አገደች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት ማገዷን ይፋ አድርጋለች።

ሞሮኮ “አንድ ቻይና” (“One-China”) ፖሊሲ ጋር የተያያዘውን የቤጂንግ አቋም የምትደግፍ በመሆኗ ከታይዋን ጋር ያለው የንግድና የጉዞ ግንኙነት እንቅፋት ገጥሞታል።

ውሳኔው የተሰማው ሞሮኮ በንጉሥ ሞሃመድ 6ኛ አመራር ስር ያስመዘገበችውን የ27 ዓመታት የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገት በታላቅ ድምቀት በማከበር ላይ በምትገኝበት ወቅት ነው።

የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እገዳውን የጣለው ሞሮኮ ቀደም ሲል ለታይዋን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን የመግቢያ ፈቃድ በማቋረጧ ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል።

የሞሮኮ ንጉሥ ሞሃመድ 6ኛ ስልጣን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ሞሮኮ በሰሜን አፍሪካ የኢንዱስትሪና የንግድ ማዕከል ለመሆን ያደረገችው ጉዞ ስኬት አምጥቶላታል።

የሁለቱ ሀገራት የቪዛ ውሳኔ በዜጎች እንቅስቃሴ እና በንግድ ልውውጥ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Taiwan #visas
#Moroccans #OneChinapolicy


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: