#Ethiopia | በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር በርሃኑ ገረሱ ክብረት ከአሜሪካ የፋርማሲ ኮሌጆች ማህበር የ”ዓመቱ ምርጥ መምህር” ሽልማት ተቀብለው በመመለስ ላይ እያሉ በዳላስ-ፎርት ዎርዝ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት እንደገለጸው ዶክተር በርሃኑ እ.ኤ.አ በሰኔ 2021 በሕጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ ቢሆንም የተቀመጠላቸው የቪዛ ጊዜ እ.ኤ.አ ግንቦት 31 ቀን 2024 ካበቃ በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ መቆየታቸውን ተከትሎ በኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አስታውቋል።
የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በሰጠው መግለጫ ድርጊቱ እጅግ እንዳሳሰበውና ዶክተር በርሃኑ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ የሚወደዱና ውጤታማ መምህር መሆናቸውን ገልጿል።
ከዚህ ቀደም በዊልያም ፓተርሰን ዩኒቨርሲቲ በሱሰኝነት መንስኤዎችና ሕክምና ዙሪያ በምርምር የሰሩት ዶክተር በርሃኑ ያለባቸው የቪዛ ስጋት በፍጥነት ተፈትቶ ወደ ተቋሙ ተመልሰው አጠቃላይ የማስተማርና የምርምር ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ ዩኒቨርሲቲው ተስፋ ማድረጉን አስታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.