የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አማካሪ የሆኑት አቶ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ሰራዊት አመራሮችና አባላት በጥቂት የህወሓት ፖለቲከኞች ተገፋፍተው ክልሉን ዳግም ወደ እልቂት ከመክተት እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።
አቶ ጌታቸው በኤክስ ገጻቸው የደብረ ጽዮንን ንግግር አያይዘው ባሰራጩት እጅግ ነቀፋ የበዛበት  መልእክት፣ የህወሓት አመራሮች የትግራይን ህዝብ አንድነት በመበተን እንዲሁም በፋኖ፣ በሱዳኑ ጄኔራል አል-ቡርሃን እና በኤርትራ መንግስት (ሻዕቢያ) ላይ ተማምነው ዳግም ጦርነት ለመክፈት የሚያደርጉት ፉከራ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ ገልጸዋል። በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ በወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) እና በቀድሞው የደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሪነት፣ በጉልበት “አራት ኪሎ እንመለሳለን” በማለት የሚያልሙትን “ቅዠት” በአስቸኳይ እንዲያቆሙ አስጠንቅቀዋል።
ከፌደራል መንግስቱ ጋር በቅርበት እየሰሩ የሚገኙት አቶ ጌታቸው፣ የትግራይ ሰራዊት ከምንም በላይ የህዝቡን ደህንነት እንዲያስቀድም ጥሪ አቅርበዋል። አቅም እያለ የህዝቡን የህልውና ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ብቻ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ሰራዊቱ በህይወቱና በአካሉ ላይ እየተቆመረበት ያለውን ኃይል ‘ይበቃል’ ሊለው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም “በሐውልቲ (የህወሓት ጽህፈት ቤት) የመሸገው የብጥብጥ ቡድን” ሲሉ የጠሯቸው እነዚህ አካላት፣ በፉከራና በውጭ ኃይሎች ድጋፍ ላይ በመተማመን የዲፕሎማሲ በሮችን ከዘጉ በኋላ፣ አሁን መሬት ላይ ያለው እውነት ሲከብዳቸው “ዓለም ይድረስልኝ” እያሉ መጮሃቸው ማመዛዘን የጎደለው የፖለቲካ ኪሳራ መሆኑን በአጽንኦት ተችተዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: