#Ethiopia | ከአስር ዓመት በፊት እንዲህ ሆነ።በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት የሚገኘው የሊማ ፖሊስ መምሪያ በፍርድ ቤት ያልቀረበውን ዶናልድ “ቺፕ” ፑግ የተባለ ተፈላጊ ግለሰብ ለማደን በፌስቡክ ገጹ የፍለጋ ማስታወቂያ አወጣ።
ነገር ግን ተፈላጊው ግለሰብ ከመሸሸግ ይልቅ በፖሊስ የወጣው የመታወቂያ ፎቶው እንደማያምርበት በመግለጽ “ይህ የተሻለ ፎቶ ነው፤ ያኛው አስቀያሚ ነው” የሚል አጭር መልእክት ከተሻለ የሰልፊ ፎቶው ጋር ለፖሊስ ልኳል።
የሊማ ፖሊስም መልእክቱን አይቶ እንዳላየ ከማለፍ ይልቅ ግለሰቡ ላደረገው “ትብብር” በፌስቡክ ገጹ ላይ አመስግኖ አዲሱን የሰልፊ ፎቶ የለጠፈው ሲሆን፣ እጁንም እንዲሰጥ አሳሰበ።
በሁለቱ አካላት መካከል የተደረገው ይህ ድንቅ ውይይት በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ ሰዎች የተጋሩት ሲሆን፣ የብዙዎችን አስገርሟል።
ዶናልድ ፑግ ከጥቂት ቀናት በኋላ በፍሎሪዳ ግዛት በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም የላከው ሰልፊ በቅርብ ዓመታት ከተመዘገቡት እጅግ አስገራሚ የፖሊስ የፍለጋ ማስታወቂያዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.