#Ethiopia | ኢራን ለእስራዔሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ የወታደራዊ ቦታዎችን መረጃ አሳልፈው ሰጥተዋል ስትል ስትከሷቸው የነበሩትን ኦሚድ ቤህዛድ እና ፑሪያ ሳፍቫት የተባሉ ሁለት ግለሰቦችን በስቅላት መቅጣቷ ተገለጸ።
በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጣቸው የሞት ውሳኔ የጸደቀው እና የተገደሉት ዛሬ ማለዳ መሆኑን የኢራን ፍርድ ቤት ልሳኖች ዘግበዋል።
በሌላ በኩል ከቅርብ ጊዜው የጥር ወር ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር የዋሉ በርካታ ታዳጊዎችና ወጣቶች አሁንም የሞት ፍርድ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።
የኢራን የሕፃናት መብት ተሟጋቾች ማኅበር እና የሕፃናት ፍትሕ ማዕከል በጋራ ባወጡት መግለጫ በቅርቡ የ20 ዓመቱ አርቪን ኼይርኻህ መገደዱን ተከትሎ የ18 ዓመቱ ሸርቪን ባገሪያንን ጨምሮ ሌሎች ወጣቶች በማንኛውም ጊዜ ሊረሸኑ ይችላሉ በሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በእስር ላይ ከሚገኙ ከ180 በላይ ታዳጊዎች መካከል ቢያንስ 14ቱ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆን ሁለቱ ከተረሸኑ በኋላ 12ቱ እድል ፈንታቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
የሰብዓዊ መብት ተቋማቱ ኢራን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በነበረበት ወቅት በተፈጸሙ ድርጊቶች ታዳጊዎችን ለሞት ፍርድ በመዳረግ ዓለም አቀፉን የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን እየጣሰች ነው ሲሉ ወንጅለዋል።
የኢራን ባለስልጣናት ግን አለብን ከሚሉት ስጋት አንጻር የሞርት ፍርዱም ሆነ ሌሎች ቅጣቶች ተመጣጣኝ ነው ባይ ናቸው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.