እስራኤል ፍልስጤማውያን ታሳሪዎችን በአዞዎችን ለመክበብ የማሠቧ ነገር ውድቅ ሆኗል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የእስራኤል ፍርድ ቤት የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን-ግቪር ፍልስጤማውያን እስረኞች በሚገኙበት የኬትዚኦት እስር ቤት ዙሪያ አዞዎችን ለማስቀመጥ አስበው የነበረውን አወዛጋቢ እቅድ በጊዜያዊነት አገደ።

ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ‘ሌት ዘ ኤኒማልስ ሊቭ’ የተሰኘው የእንስሳት መብት ተሟጋች ቡድን ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ነው።

ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ የታቀደው አሰራር በእንስሳቱ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ተብሎ የቀረበው ስጋት በደንብ ሊመረመርና ሊፈተሽ እንደሚገባ በማሳሰብ እቅዱ እንዳይፈጸም እግድ ጥለውበታል።

የተገበረውን የሰው ልጅ በአውሬ ከቦ ማሠር ከሰብዓዊ መብት አንጻር ምን አንድምታ እንዳለው ግን የተባለ ነገር የለም።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2