#Ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት በብራዚል የሕዝብ ጤና ዘርፍ ላይ እያፈሰሰ ያለው ዘላቂ መዋዕለ ንዋይ ለሚሊዮኖች ዜጎች የጤና አቅርቦትን በከፍተኛ ሁኔታ እያሰፋ መሆኑን በመግለጽ የሀገሪቱን ጥረት አደነቀ።
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ጋር በመሆን በሪዮ ዲ ጃኔሮ የሚገኘውን የአንዳራኢ ፌደራል ሆስፒታል የጎበኙ ሲሆን በሆስፒታሉ የተደረገው ዘመናዊ መሣሪያዎችን የማሟላት የአገልግሎት ማስፋፋትና የጤና ባለሙያዎችን የማጠናከር ሥራ እጅግ አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ እንቅስቃሴ ብራዚል የተዋሃደ የጤና ሥርዓቷን ለማጠናከር የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል ሲሆን የካንሰር ሕክምናን ከማስፋፋት በተጨማሪ በተንቀሳቃሽ የሕክምና ክሊኒኮች እና በ1,200 አዳዲስ ተንቀሳቃሽ የጥርስ ሕክምና ክፍሎች አማካኝነት የጤና አገልግሎቱን ወደ ማህበረሰቡ እያቀረበች ነው።
እስካሁን በተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች ከ613 ሺህ በላይ ሰዎች የካንሰር መከላከያ የዓይንና የምስል ምርመራ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን አዳዲሶቹ የጥርስ ሕክምና ክፍሎች ደግሞ በየዓመቱ ከ4.3 ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ሰዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም አላቸው።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የብራዚሉ ፕሬዝዳንድ የጥርሳቸውን ደህንንነት ሲመለከቱ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ድህረ ገጻቸው የለጠፉ ሲሆን የብራዚል መንግስት ጥንካሬ ያለው የሕዝብ ጤና ሥርዓት ሕይወትን እንደሚያድንና ማህበራዊ እኩልነትን እንደሚያረጋግጥ በመጠቆም ድርጅታቸው ብራዚል ለሁሉም ዜጎቿ የጤና አገልግሎትን ለማድረስ የምታደርገውን ጉዞ መደገፉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.