#Ethiopia | “ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለመሬት አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች፡፡”

- Advertisement -
Sidebar AD

– የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
እናት አለም መለሰ

***
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተዘጋጀው ታሪካዊ ሀገራዊ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ያቀደችውን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ ጀምራለች።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በሰጡት መግለጫ፣ መላው ኢትዮጵያውያን የተጎሳቀለችውን ምድር ለመመለስና ለቀጣይ ትውልድ ዘላቂ አሻራ ለማኖር በአንድነት መነሳታቸውን ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ፣ “ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለምድር አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች” በማለት የሕዝቡን የአንድነት መንፈስና ለተፈጥሮ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በ“ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው የዘንድሮው ዘመቻ፣ በመደመር መርህ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በንቃት እንዲሳተፉና 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን የመትከል ግብ እንዲሳካ ጥሪ ቀርቧል።

መርሐ ግብሩ ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም. እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ሁሉም ክልሎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በሰፊው እንደሚከናወን ተገልጿል።

ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአካባቢ ጥበቃ፣ የደን ሽፋን መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እና ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለማስረከብ ከሚደረጉ ሀገራዊ ጥረቶች መካከል ቁልፍ ተነሳሽነት መሆኑ ተጠቅሷል።

#አረንጓዴአሻራ #GreenLegacy #Ethiopia #PlantTrees #ClimateAction #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: