እኔ ውሸታም ወይም አታላይ አይደለሁም!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ጄሰን አርደይ የሌሎች ምሁራን ጽሑፎች ያለ አግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ ቀረበባቸው።

ክሱ በዋናነት የተነሳው በፈረንጆቹ 2015 ባዘጋጁት የመመረቂያ ጽሑፏቸው ላይ ሲሆን በዚህ ጽሁፋቸው የምሁራን ጥናቶች በቀጥታ ያለ ምንጭ ተጠቅመዋል የሚል ነው።

ፕሮፌሰሩም በፒኤችዲ ቴሲሳቸው እና ባሳተሟቸው አካዳሚያዊ ጥናቶች ላይ የቀረበባቸውን የጽሑፍ ስርቆት ክስ አስተባብለዋል።

ፕሮፌሰሩ በጥናቶቻቸው ላይ ጥቂት የአሰራር እና የቴክኒክ ስህተቶች መከሰታቸውን አምነው እኔ ግን ውሸታም ወይም አታላይ አይደለሁም ሲሉ ራሳቸውን ተከላክለዋል።

በቀደሙት ሥራዎቼ ላይ የቴክኒክና የምንጭ አጠቃቀም ስህተቶች መኖራቸውን እቀበላለሁ ለሰራኋቸው ስህተቶችም ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብለዋል።

ነገር ግን አካዳሚያዊ ማጭበርበር ወይም የፁሁፍ ስርቆት ፈፅመሀል የሚለው ውንጀላ ፍፁም ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በሰጠው መግለጫ የቀረቡት አቤቱታዎች ላይ ጥልቅ ምርመራ መደረጉንና ፕሮፌሰሩ ምንም የፈፀሙት ስህተት የለም ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ውንጀላውን የፕሮፌሰሩን ስም ለማጠልሸት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ሲል ገልጾታል።

በተጨማሪም በርካታ ምሁራንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለፕሮፌሰሩ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

ክሱ በጥቁር ምሁራን ስኬት ላይ ያተኮረ ፖለቲካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጫና እንደሆነ ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#England
#Cambridgeuniversity
#professor


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1