በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️
በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከደረሱበት አሰቃቂ ጥቃቶች ሳያገግምና ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።
በትግራይ ክልል ያገረሸው ግጭት ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ጋር ተደማምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየደረሰ መሆኑን የገለጸው አምነስቲ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካላትን ሥራ በአስቸኳይ መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በጥፋተኞች ላይ ምርመራ እና ክስ ያለማቅረብ አካሄድ ልማዳዊ ሊሆን አይገባም ብሏል።
የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ለነጻ የሰብአዊ መብት ተከታታዮች፣ ለሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች እና ለገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ፈቃድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.