የታጠቁ ኃይሎች አራት ኪሎ ባዶ ሁኖ “ኑና ቤተመንግሥት ግቡ” ቢባሉ ወደ አዲስ አበባ አይመጡም‼️
👉 የመከላከያ ከፍተኛ መኮንን የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጀነራል አምባሳደር #ባጫ_ደበሌ ከቢቢሲ አማርኛ (BBC News Amharic) ጋር ያደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ የተገለፀ ሲሆን፤ ቢቢሲ ከቃለ-መጠይቁ አጠር አድርጎ ያወጣው አነስተኛ የቪዲዮ ምስል ቀጣዩን አቅጣጫ ጠቋሚ በመሆኑ በድጋሚ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
በዚህ አጭር መግለጫቸው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ የታጠቁ ግጭቶች ከመጨራረስ ውጭ ምንም ዓይነት ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ያስገነዘቡት ጀነራል አምባሳደሩ፤ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ አካላትን አቅም አስመልከተው ሲናገሩም “አራት ኪሎ ክፍት ሆኖ ኑና ግቡ ቢባሉም እንኳን #ፋኖም ሆነ #ኦላ (ጃል መሮ) አይመጡም፤ መጥተውም የሚያደርጉት ነገር የለም” ሲሉ ገልፀዋል።
አክለውም፤ “እንደ #ዘመነ_ካሴ ያሉ የውጊያ መሪዎች መጥተው አራት ኪሎ የመግባትና ሀገር የመምራት አቅም የላቸውም” ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በጦርነት ውስጥ አሸናፊና ተሸናፊ የሚባል ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ጀነራል አምባሳደሩ፣ “የታጠቁ ኃይሎች ገንዘብ ከፈለጉ ከመንግስት ይውሰዱና ህዝቡን ይተውት” ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ካልሆነ ግን የትግሉ መጨረሻ የህዝብና የሀገር መጨራረስ ብቻ ሆኖ እንደሚቀርና ማንኛውም ወገን የፖለቲካ ማተርፊያ እንደማያገኝበት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.