“ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት፤
ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ “ማቴ 26፡40
የበአታ ገዳም መልዕክት
ይህን ታላቅ ጾም በታላቋ ገዳም በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካነገሥት በአታ ለማርያም በደብረመንክራት
ሥዕልቤት ኪዳነምህረት ገዳም ፡፡
ይህ ጾመ ማርያም (ጾመ ፍልሰታ) ከ7ቱ ታላላቅ አጽዋማት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል ይህን ጾም ከሌላው
ለየት የሚያደርገው አባቶቻችን ሐዋርያት ለትምህርተ ወንጌል ከተሰማሩበት ተሰባስበው የእመቤታችንን
ትንሳኤዋንና ዕርገቷን ለማየት ሁለት ሱባኤ ወይም ለ14ቀን ፈጣሪያቸውን በጸሎትና በምህላ ጠይቀው
ትንሳኤዋን እና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል፡፡እኛም የእነሱን መንገድ ተከትለን በቤተ እግዚአብሔር በጸሎት
በቅዳሴ በሰዓታት በምህላ ለሁለት ሱባኤ ወይም ለ14ቀን በየዓመቱ ሱባኤ ይዘን እንጸልያለን፡፡ ይህ ጾመ ሱባኤ
በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም በስዕል ቤት ኪዳነምህረት ገዳም በልዩ ሁኔታ ይከናወናል፡፡ ሆኖም አሁን
ባለው ሁኔታ በገዳማችን አካባቢ የሚገኙ ምእመናን በመልሶ ማልማት ምክንያት ከስፍራው ርቀው ይገኛሉ ፡፡
ስለሆነም ይህ የጥሪ መልእክት የደረሳችሁ ምእመናን እና ምእመናት በሙሉ በገዳማችን መጥታችሁ ይህን
ታላቅ የሱባኤ ጾም እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡
በሱባኤ ጊዜ በገዳማችን የሚከናወኑ መንፈሳዊ የሱባኤ አገልግሎቶች
1ኛ. ከምሽቱ 4ሰዓት እስከ ጠዋት 12፡30 የሰዓታት ቁመት ኪዳንን ጨምሮ ይከናወናል፡፡
2ኛ የውዳሴ ማርያም እና የቅዳሴ ማርያም ትርጉም ከ3፡30 እስከ 6፡00ሰዓት የካሄዳል፡፡
3ኛ ከ6፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ሰዓት የቅዳሴ አገልግሎት በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል፡፡
4ኛ በገዳማችን ብቻ በተለየ መልኩ የሚጸለይ የሠርክ ጸሎት (የምህላ) አገልግሎት መሐረነአብ ተብሎ
እግዚኦ መሐረነክርስቶስ መቶ ጊዜ በእንተማርያም መሐረነክርስቶስ መቶ ጊዜ እየተባለ ከ9፡30 እስከ 11፡00
ሰዓት ይደረሳል ፡፡
5ኛ ከ11፡00 እስከ 12፡30 የትምህርተ ወንጌል መርሀ ግብር ይፈፀማል፡፡
ይህንን ጾመሱባኤ በእመቤታችን በበአታማርያም ደጅ መጥታችሁ በታላላቅአበው መነኮሳት እጅ
እየተባረካችሁ በመጨረሻም ነሐሴ16 ቀን በዚሁ ገዳም የኪዳነምህረት በአለንግሧን አንግሣችሁ በረከት
እንድታገኙ ጥሪያችንን በእግዚአብሔርስም እያስተላለፍን በበአታ ገዳማችን ተገኝታችሁ እንድትጸልዩ
ተጋብዛችኋል ፡፡
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.