ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የሰረቀው የሆስፒታሉ ጥበቃ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣተከሳሽ እንድሪያስ ቶማስ ግያ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የሰረቀው የሆስፒታሉ ጥበቃ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ እንድሪያስ ቶማስ ግያ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪና ሪፈራል ሆስፒታል የጥበቃ ሠራተኛ ሆኖ እየሰራ ሀምሌ 22  ቀን 2018 ከምሽቱ 4:00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።
የሆስፒታሉ ንብረት የሆነውን ሶስት ማይክሮስኮፕ የእያንዳንዳቸዉ ዋጋ ሶስት መቶ ሀምሳ ሺ  ብር በድምሩ አንድ ሚሊዮን ሀምሳ ሺ ብር የሚያወጣዉን ከክፍሉ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ንብረቱ ያለበትን ክፍል በቁልፍ ከፍቶ ከወሰደ እና ንብረቱን በተቋሙ ዉስጥ ባለዉ ሳርና ሀረግ ዉስጥ ደብቆ ካቆየ በኋላ ሀምሌ 25 ከሌሊቱ 9 ሰዓት ንብረቱን ካቆየበት ሥፍራ አንስቶ እየወሰደ እያለ ከንብረቱ ጋር የተያዘ ስለሆነ ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሷል ።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ዐ/ሕግ  ያቀረበውን ክስ ሲያከራክር የቆየው የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ ያመነ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ያመነ መሆኑን፣ የቤተሰብ አስተዳደር እንዲሁም ቀደም ስል የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በ7 አመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ውሳኔ አሳልፎል።
የተሰረቀው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዋጋ የሚያወጣው ማይክሮስኮፕ ለኦቶና ሪፌራል ሆስፒታል ተመላሽ መደረጉን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮሚኒኬሽን አስታውቋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: