ኢትዮጵያዊቷን አትሌት ወደ ወንድ የሚያደላ የሆርሞን መብዛት አለባት በሚል ምክንያት ወደ አሜሪካ ሳትጓዝ ቀረች።
የፆታ ውዝግብ( የሆርሞን መብዛት ) ያለባት ኢትዮጵያዊት አትሌት ወደ አሜሪካ አልተጓዘችም ። በጋና አክራ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ400ሜ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችውና በአሁኑ የአሜሪካ ኦሪገን….
ዩጂን ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጠንካራ ዝግጅት ስታደርግ የቆየችው እንዲሁም ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጣት አጃይባ አሊየ ወደ አሜሪካ ሳትጓዝ ቀርታለች።
አትሌት አጃይባ በሻምፒዮናው ላይ እንድትወዳደር ስም ዝርዝሯ የገባ እና የአሜሪካ ቪዛ ተሰጥቷት ነበር።
ለሲዲ ስፖርት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ባለሙያ አትሌቷ ከፆታ ውዝግብ ማለትም (ወደ ወንድ የሚያደላ የሆርሞን መብዛት) ጋር በተገናኘ ወደ ስፍራው ሳትሄድ ቀርታለች ማለታቸውን ጋዜጠኛ ሶፎንያስ እና ጋዜጠኛ ግርማቸው ተናግረዋል ።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያኖቹ ፋንቱ ሜጌሶ እና ወርቅ ውሃ ጌታቸው እንዲሁም ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰሜንያ በተመሳሳይ ጉዳይ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር አይዘነጋም ።
በሌላ በኩል ደግሞ የአትሌት አጃይባ ስም ውድድሩ ቦታ መለጠፉ ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና አጋፋሪዎቹ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ምክንያት ማቅረብ ሌላ ተጨማሪ ጥፋት ነው ።
ጉዳዩ ፈጣንና አስተማሪ እርምጃ ከሚመለከተው አካል ይሻል ትልቅ እድል ነው ያገኘችው በፍጥነት መፍትሔ ማግኘት አለባት ።
@Seledadotio

No comments yet.