በትግራይ «70 ካሬ» የተፈናቃዮች ማዕከል በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ ከ20 በላይ ጊዜያዊ መጠለያዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በትግራይ «70 ካሬ» የተፈናቃዮች ማዕከል በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ ከ20 በላይ ጊዜያዊ መጠለያዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡
የምዕራብ ትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (ፅላል) አስተባባሪ አቶ ዘበኖም ኪዱ ለትግራይ ቲቪ እንደገለጹት፤ ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ መጠለያዎቹ ከጥቅም ውጪ ከመሆናቸውም በላይ በንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል።
በተጨማሪም አደጋው በሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ በተለይም አረጋውያን ላይ ጉዳት በመድረሱ ለሕክምና እርዳታ ወደ ጤና ተቋም መወሰዳቸውን አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል።
በደረሰው አደጋ ምክንያት ተፈናቃዮቹ ለበለጠ እንግልት እና ችግር መጋለጣቸውን የጠቆሙት አቶ ዘበኖም፣ የሰብአዊነት ስሜት ያለው አካል ሁሉ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የተፈናቀለው ሕዝብ በከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ያመለከተው የምዕራብ ትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፣ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው ተፈናቃዮች ወደ ቀደመ መኖሪያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ሲመቻች ብቻ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቷል ሲል ዘገባው መልክቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2