#Ethiopia | እስራኤል በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎችን በ2027 አገልግሎቱን በይፋ ልታስጀምር ነው።
እስራኤል ይህንን አገልግሎት አስቀድማ ለማስጀመር ከባለፉት አምስት አመታት ጀምራ ጥረት ስታደርግ ነበር ሲል ዘ ጀሩሳሌም ፖስት የዘገበው።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች የራሳቸውን የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ባለፉት አምስት ዓመታት ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም ወጥ የሆነ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂና የደህንነት ስታንዳርድ ባለመኖሩ ምክንያት ሂደቱ ሲጓተት ቆይቷል ነው የተባለው።
ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተሽከርካሪዎች ህግ አውጪ አካል በቅርቡ ያጸደቀው አዲስ የደህንነትና የቁጥጥር መመሪያ አገልግሎቱ ለማስጀመር ረድቷል ተብሏል።
አዲሱ የሕግ ማዕቀፍ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ከሰው አሽከርካሪ ያላነሰ ወይም የተሻለ የደህንነት ብቃት ሊኖራቸው እንደሚገባ ያስገድዳል።
በዚህም መሰረት አዲሱ የአውሮፓ ስታንዳርድ እስራኤል ውስጥ በቀጥታ ተግባራዊ የሚሆን ይሆናል።
የእስራኤል የትራንስፖርት ሚኒስቴር ያለ አሽከርካሪ የሚሰሩ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ለአስመጪዎች ፍቃድ ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት እያፋጠነ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Israel #taxi
#transport #technology
Source: GetuTemesgen








No comments yet.