ከአፍጋኒስታን እስከ ዚምቧብዌ

- Advertisement -
Sidebar AD

የተደረገ የሞት ሽረት ጉዞ

የአለም ሀገራትን በሙሉ ያካለለችው 21 አመቷ ሶፊያ

#Ethiopia | በ17 አመቷ በአለም ሀገራት ጉብኝት ማድረግ የጀመረችው ሶፊያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተመዘገቡ 195 ሀገራት መካከል ያልጎበኘቻቸው አራት ሀገራት ብቻ ነው።

በ17 ዓመቷ የጀመረችውን አስደናቂ ጉዞ ማጠናቀቂያ ላይ የምትገኘው ሶፊያ ሊ ሁሉንም የዓለም ሀገራት በመጎብኘት ከዓለም በዕድሜ ትንሿ ሰው የሚለውን የዓለም ድንቅ መዝገብ ላይ ለመስፈር ጫፍ ደርሳለች።

ሶፍያ የአለም ሀገራት ማካለል ብቻ ሳይሆን እጅግ ተቃራኒ የሆኑ ባህሎችንና የፖለቲካ ሁኔታዎችን ማስተናገድን ያካተተ ነበር።

አሁን ላይ አብዛኞቹን የዓለም ሀገራት አጠናቃ የመጨረሻ እና ፈታኝ የተባሉትን መዳረሻዎች በመጎብኘት ላይ ትገኛለች።

በጉዞዋ ወቅት ከእስያ እስከ አፍሪካ ከአፍጋኒስታን አስቸጋሪ ሁኔታዎችና የደህንነት ስጋቶች ጀምሮ እስከ ደቡብ አፍሪካ እና ኡጋንዳ የተፈጥሮ ድንቆች ድረስ ተዟዙራለች።

ሶፍያ በመጨረሻ ጎዞዋ እንደ ማሊ ቻድ ቬኔዙዌላና ዚምቧብዌ ያሉ ለማለፍ ከባድ እና አስቸጋሪ የሆኑ ሀገራትን በመጎብኘት ታሪካዊ ጉዞዋን በቅርቡ ለማጠናቀቅ አቅዳለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Sophia #unitednation
#Worldrecord


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: