የግብር ገዳይ‼️
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፤ አነስተኛ ንግዶችን ለመደገፍ የግብር ሥርዓት ማሻሻያ እየተደረገ ነው አለ።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አነስተኛ ነጋዴዎችን ለማበረታታት፣ የግብር ጫናን ለመቀነስና ትርፋማነታቸውን ለማሳደግ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን እየተገበረ መሆኑን ገለጸ።
ቢሮው ባለፉት ሁለት ዓመታት ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የመልካም አስተዳደር ክፍተቶችን ለመቅረፍና ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸውን አስታውቋል።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች፣ በኪራይና በራይድ ትራንስፖርት የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ 9.2 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጿል።
ቢሮው አነስተኛ ነጋዴዎች በግብር ጫና ሳይጎዱ ወደ ትልቅ የንግድ ደረጃ እንዲያድጉ የድጋፍ ሥርዓቶችን እያጠናከረ መሆኑንም አመልክቷል።
በ2018 የግብር ዘመን አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች በተዘረጋው የኦንላይን ክፍያ ሥርዓት ግዴታቸውን እየተወጡ ሲሆን፣ ቅሬታ ያላቸው ግብር ከፋዮች ደግሞ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘረጋው የቅሬታ ማስተካከያ ሥርዓት መፍትሔ እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቋል።
በቀጣዩ 2019 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ 502.27 ቢሊዮን ብር፣ የገቢዎች ቢሮ ደግሞ 380 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጿል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.