የጨቅላዋ ህጻን ጥቃት እና ሲቃ

- Advertisement -
Sidebar AD

የህጉ ክፍተት ወይንስ የአፈጻጸም ችግር ?

1. የጹሁፌ መግቢያና የህጻናቱ የፍትህ ጥሪ

#Ethiopia | ህጻናት ወደዚህች አለም ሲመጡ ሙሉ ስነህይወታዊ እና ተፈጥሮአዊ ስነልቦናን ይዘው የእናትንና አባትን እቅፍ ለአፍታም እንዲለያቸው ሳይሹ በሌላው እድሜ ከሚገኙ ይልቅ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ የሚፈልጉ የተፈጥሮ ስጦታ የሆኑ የዚህ አለም አዲስ ትውልድ ጌጥ ናቸው። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰማን ጆሮአችንም ተለማምዶት ባይሆን ውስጣችንም ጨክኖባቸው ካልሆነ በእነርሱ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት “አረ በምን ችለውት” ተብሎ ለማሰብ እስከሚሰቀጥጥ ድረስ በተለያያ ቦታ ሴት ህጻናት እየተደፈሩ እኛም እየሰማን እያለፍነው እየተለማመድነው የመጣን ይመስለኛል።

አይደለም ህጻናት ሊደፈሩ ቀርቶ እንዲሁም ሀሳባቸውን መግለጽ በማይችለው አንደበታቸው የተቆራረጠ ቃላትን ከአሳዛኝ አይናቸውና ፊታቸው ጋር ሆነው ስሜታቸውን ከመግለጽ ውጭ ፣ እንዲሁ ሲያይዋቸው የሚያሳሱ የፈጣሪ አምሳያዎች ይህ ጥቃት ተፈጽሞባቸው ስንሰማ ይህንን ድርጊት ሲፈጸም በሚፈለገው ልክ ሳናወግዝ ልጄ ልጄ እያልን ከእነርሱ ጋር እያቀፍን መጫወታችን አለማፈራቸን ይህን ቢያውቁ እና ቢረዱ ይህን የህጻናት አስገድዶ መድፈር እና ፍጹም የአውሬ ተግባር በወንጀሉ ልክ ሳታወግዙ ፣ ሳትከላከሉ እናንተንስ ከእነዚህ ሰው በላዎች በምን ተሻላችሁ? ምንስ ዋስትና አለን?

ብለው ራሳቸውን ከእኛ የሚያገልሉ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡ ወይንም እኛ የማናውቀውን እነርሱ የሚያውቁትን የተለየ ነገር የሚያደርጉ ይመስለኛል። እኔም ለዛሬ ይዤላችው የቀረብኩት ህጻናቱ የመደፈራቸውን የወንጀል ጫና ወደ ውስጤ በአንዳች ነገር በሰመመን ከጨቅላ ደም አካላቸው በጥቃታቸው ምክንያት የሰቆቃን እንባን በማቃሰት እያነቡ ከሚፈሳቸው የጥቃት ጥሪ ድንገት አቃጭሎብኝ ይህቺን ልጽፍ ተገድጃለው።

2. ህጻን ማን ነው?

ህጻን ማለት በአለምአቀፍ የህጻናት መብት ስምምነት/ህጎች/ እንዲሁም በሀገራችን ባሉን ህጎች ከ18 አመት በታች ቢሆንም
ከሚሰጣቸው የመብት ትኩረት አንጻር ግን ከሚደርስባቸው ጥቃት ጋር ሲነጻጸር ሰባት እና አምስት አመት እንዲሁም ከዚህ በታች የሆኑ ሴት ህጻነት ተደፈሩ እየተባለ በየማህበራዊ ሚዲያ የምንሰማው ጉዳይ ለማመን የሚከብድ ሲሆን እኔስ በዚህ ጹሁፌ ትኩረት የሳቡኝ እና በአይነህሊናዬ በደም በተነከሩ ልብሶቻቸውና እና ሰውነታቸው ሆነው ሰው አይሉት አውሬ በሆነ ሰው መሠል ፍጡር እንዳሻው ከአይነ ህሊናቸው እና ከሰውነታቸው የማይደን ቁስል አትርፎባቸው የፈለገውን ሆኖ ለሚጫወትባቸው የሰቆቃ ድምጻቸውን ለሚያሰሙኝ የሰባትና አምስት አመት እድሜ ከዚህ በታች ለሆኑት እንቦቅቅላቸች ህጻን የሚለውን ትርጉም ሰጥቼ በዚህ ጹሁፍ ቀርቢያለው።

3. የህጉ ወይንስ የአፈጻጸም ችግር

በዚህ ላይ በተለያየ ጹሁፍ የተለያየ ሀሳብ የተሰጠበት ሲሆን ፈጣሪ ጊዜ እና እድሉን ሰጥቶን ተጨባጭ ከሆኑ የህጻናት መብት አጠባበቅ እና አፈጻጸም ከእነችግሮቹ እና መፍቴዎች ጭምር ወደፊት ለማቅረብ ጽኑ ፍላጎቴ ሲሆን ለአሁን ግን በህጻናት መብት አጠባበቅ ላይ ያለው ህግ ብዙ ትችት የሚሰነዘርበት እና በተለይም ከሴት ህጻናት ከጠቀስናቸው እድሜ አንጻር የሚደፈሩ ህጻናትን ህጉ በተለየ ሁኔት ጥበቃ የማያደርግና ይህ ክፍተት ሲሆን ወደ ፊት ሊሻሻል የሚገባው አብይ ጉዳይ ሆኖ ፥ በህጉ አፈጻጸም ረገድም ከፍተኛ ችግር ያለበት ነው።

የህግ ባለሙያዎች ፣ የፍትህ አካላት ፣ ማህበረሰቡ ፣ የህጻናቱ አሳዳጊ የሆኑ እናት አባት ቤተሰብ ሁሉም በየድርሻው የራሱ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን በመንግስት የፍትህ አካላት አቅጣጫ አጠቃላይ ማህበረሰቡን ያሳተፈ የህግ እና አፈጻጸም ሊኖር እና መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል?

4. እኚህ ህጻናት ምን ይላሉ?

እነዚህ በእድሜ ከሰባትና አምስት ያልዘለሉ ሴት ህጻናት በጥበቃና እንክብካቤ ልልነት እና ሰበአዊነትን በማጣት በአረሜናዊ ድርጊት አሁንም አሁንም የሚደርስባቸው ጥቃት አይሎ እባካችሁን ድምጽ ሁኑን ሲሉ በዚህ ጹሁፍ ይጮሀሉ ፤ ይናገራሉ።

5. ከእኛ ምን ይጠበቃል?

ሁላችንም ከራሳችን ጀምሮ ሴት ህጻናት ልጆቻችንን አስፈላጊውን እንክብካቤ እና ጥበቃ በማድረግ ከሚውሉበት ቦታ አከባቢ ጥብቅ መረጃ ክትትል ማደረግ፣የሚውሉበትን ኃላፊነት መጠን እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ማወቅ፣ ለማህበረሰቡ በቂ የህግ ግንዛቤ እንዲኖር አስፈላጊውን ማድረግ፣የህግ ክፍተቶች እንዲሟሉ ተገቢውን ግፊት ማድረግ፣ የሴቶች ህጻናት ጉዳይ ላይ የማህበረሰቡ ተሳትፎ እንዲጠነክር ከነቃ ውይይት ጀምሮ ጥረት ማድረግ፣የህግ ባለሙያዎች በተለይም በዚህ ዘርፍ ላይ ያሉ ህጻናት ልዩ እውቀትና ልምድ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ የህግ አፈጻጸም በዚህ ረገድ ተጠናክሮ እንዲያድግ አስፈላጊውን ትብብር ከመንግሥት ድጋፍ ጀምሮ ሁሉም የተሳተፈበትን ተግባር መፈጸም ያስፈልጋል።

6. የዚህ ጹሁፍ ማሰሪያ
በየቀኑ እየተደፈሩ ላሉ ሴት ህጻናት ልጆቻችን ድምጽ እንሆን ዘንድ ይህንን ጹሁፍ በማጋራትና የሴት ህጻናት ላይ የሚፈጸመውን ወንጀል እና መደፈር እንዲቆም በማድረግ የድርሻችን ልንወጣ ያስፈልጋል።
https://www.facebook.com/share/1BKURdsCCj/
https://t.me/Fantahunlawyer
የህግ ባለሙያው ፋንታሁን ደለለው
delelewfantahun2010@gmail.com


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1