ቴሌቲቪ ተመርቆ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ድንቅ እና የተመረጡ የሀገራችንን የአማርኛ ፊልሞች ለተመልካች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። አሁንም በተመሳሳይ አዳዲስ እና አዝናኝ ፊልሞችን በመተግበሪያው (App) ላይ ይዞላችሁ መጥቷል።
በዚህም መሠረት «ዲያስፖራው» እና «ሹምሽረት» የተሰኙት አዳዲስ ፊልሞች ሐሙስ መጋቢት 30 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በቴሌቲቪ መተግበሪያ ላይ መታየት ይጀምራሉ።
ዲያስፋራው
የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው «ዲያስፖራው» ፊልም፣ ተወዳጁ ተዋናይ አለምሰገድ ተስፋዬ ከ6 ዓመታት ቆይታ በኋላ የተወነበት ድንቅ ሥራ ነው። በተጨማሪም በበርካታ ፊልሞቿ የምናደንቃት ተዋናይት ማክዳ አፈወርቅ ከ10 ዓመታት በኋላ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪው የተመለሰችበት ሲሆን፤ ታዋቂዋ ቲክቶከር ባምቢ ሀበሻ (ሐና ግደይ) ለመጀመሪያ ጊዜ የሠራችበት እንዲሁም ተሻለ ወርቁ እና ሌሎችም ተዋንያን የተሳተፉበት አዝናኝ ፊልም ነው። በተጨማሪም በሲኒማ ቆይታውም ከ6 ወር በላይ በመታየት ሪከርድ መስበር የቻለ ተወዳጅ ፊልም ነው።
ሹምሽረት
በወንዶች ጉዳይና በሌሎች በርካታ ፊልሞች ተወዳጅነትን ያተረፈው ተዋናይ አድማሱ ከበደ ፈታኝና ጥሩ የታሪክ ፍሰት ያለው ስክሪፕት በማጣቱ ምክንያት ከሲኒማው ለረጅም ጊዜ ርቆ ከቆየ በኋላ፣ በቅርቡ በዩልያን ተክለማርያም ተደርሶ በተዘጋጀው “ሹም ሽረት” በተሰኘው አዲስ ፊልም ወደ ፊልም ተመልሷል። በዚህ ፊልም ላይ አንጋፋዋ ተዋናይት ፍቅርተ ደሳለኝ በተለየ ገጸ-ባህሪ የተሳተፈች ሲሆን፣ በተጨማሪም ማስተዋል ወንደሰን እና ሌሎችም ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
እነዚህን 2 ፊልሞች ሐሙስ ዕለት በቴሌቲቪ መተግበሪያ ጠብቋቸው!
ቴሌቲቪን ለማውረድ
https://teletv.et/download
Source: Yeneta Tube








No comments yet.