በመዝናኛ ሰበብ ገብቶ መውለድ ዜግነት አያሰጥም! – ትራምፕ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከአሜሪካ ህገ መንግስት መሰረታዊ ድንጋጌዎች ጋር በቀጥታ የሚጋጨውን አዲስ ውሳኔ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጎብኚዎች የአሜሪካን ፓስፖርት በአቋራጭ የሚያገኙበትን አሰራር ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት ታስቦ ነው ብለዋል።

ይህ የትራምፕ ውሳኔ በተለይም በቱሪዝም በንግድ ወይም በጊዜያዊ ቪዛ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የውጭ ሀገር ዜጎች በሚወልዷቸው ህጻናት ላይ የሚሰጠውን የአሜሪካ ዜግነት የሚያስቀር ነው።

ጎብኚዎች ለመዝናኛና ለጉብኝት ወይም በጊዜያዊ ፍቃድ ገብተው በመውለድ የህጉን ክፍተት በመጠቀም የአሜሪካ ዜግነት የሚያገኙበትን መንገድ ከእንግዲህ ተዘግቷል ሲሉም ተናግረዋል።

በአሜሪካ ህገ መንግስት መሰረት በማንኛውም የአሜሪካ ግዛት ውስጥ የተወለደ ልጅ የወላጆቹ የስደት ህጋዊነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ልጁ የአሜሪካ ዜግነት ይሰጠዋል ይላል።

የትራምፕ አዲስ ትእዛዝ ይህንን የዘመናት ህግ በቀጥታ የሚቃረን መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

የህግ ባለሙያዎች እና የሰብአዊ መብት ተቋማት የትራምፕ አዲስ ትእዛዝ ህገ-መንግስቱን የጣሰ ነው በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

የCNBC ዘገባ እንደሚያመለክተው የፕሬዚዳንቱ አዲስ ውሳኔ ይፋ ከሆነበት ሰዓት ጀምሮ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በህግ አውጪዎች እና በሲቪል መብት ተቋማት ዘንድ የህግ ክስ ሊመሰረትበት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ሲል ፅፏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Usa #BirthTourism
#Birthright #DonaldTrump
#Constitution #amendment


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1