#Ethiopia | በፖርቶ ሪኮ ከ120 አመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ለ48 ሰአታት ያህል የቧንቧ ውሃ መቋረጡ ተነገረ።
በአካባቢው ያለው አሮጌና ለዘመናት በቂ እድሳት ያልተደረገለት የውሃ መስመር መሰረተ ልማት ችግሩን የበለጠ አባብሶታል።
በግዛቲቷ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ለ48 ሰዓታት ያህል ከቧንቧ ውሃ ርቀዋል ተብሏል።
በዋና ከተማዋ ሳን ሁዋን እና በዙሪያዋ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች የሚኖሩ ከ180,000 በላይ ዜጎች ለ48 ሰዓታት ያህል ውሃ በፈረቃ እንዲያነኙ ተደርጓል።
የአካባቢው ባለስልጣናት እና የአየር ንብረት ባለሙያዎች እንዳሉት አሁን እየተመዘገበ ያለው ከባድ የሙቀት መጠን የሚቀጥል ከሆነ ነዋሪዎች ያለ ቧንቧ ውሃ የሚቆዩበት ጊዜ እስከ 72 ሰዓታት ሊራዘም ይችላል ብለዋል።
የግዛቲቱ ዋና ገዢ ጄኒፈር ጎንዛሌዝ እንደገለጹት ሁኔታው ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው ሲሉ የአየር ንብረት መዛባቱ ሁኔታውን እንዳባባሰው ገልጸዋል።
የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች ለሆስፒታሎችና ለወጣቶች/አረጋውያን መኖሪያዎች በቦቲ ውሃ በማደል ቅድሚያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Usa #PuertoRico
#water #shutoffs
Source: GetuTemesgen







No comments yet.