“ዋንጫውን የሸጥኩት ቁምሳጥኔ ጠቦኝ ነው” – ቤንጃሚን ሜንዲ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ቤንጃሚን ሜንዲ በ2018 እ.ኤ.አ ያሸነፈውን የዓለም ዋንጫ ምስለኔ (replica) በጨረታ መሸጡ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሜንዲ ይህን ክብር ያለው የዋንጫ ቅጂ በጨረታ ያቀረበው ሲሆን፣ በጨረታውም በግምት 54,000 ዩሮ ገደማ መሸጡ ተገልጿል።

​የተጫዋቹ እርምጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ያስከተለ ሲሆን በርካቶች ይህንን መሰል ታሪካዊና ክብር ያለው ዋንጫ መሸጥ አልነበረበትም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

ሆኖም ለተሰነዘሩበት ትችቶች በቀልድ የታጀበ ምላሽ የሰጠው ሜንዲ፣ “ለመሆኑ ዋንጫው የእኔ ነው ወይስ የእናንተ? ዋንጫው የእኔ በመሆኑ በፈለግኩት መንገድ የማድረግ መብት አለኝ፤ ደግሞም በቁምሳጥኔ ውስጥ አላስፈላጊ ቦታ አጥቦብኝ ነበር” ሲል ለተነሳው ውዝግብ ግድ የለሽነቱን አሳይቷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: