የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 118 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘየተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) በሰጡ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 118 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) በሰጡት መግለጫ ÷ ገቢው ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ከኢነርጂ ሽያጭ 75 ነጥብ 17 ቢሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ የውጭ ሀገር ሽያጭን ጨምሮ 76 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡ 
በተጨማሪም ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ 37 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 39 ነጥብ 23 ቢሊየን ብር መገኘቱን ነው የገለጹት፡፡
የማያገለግሉ ንብረቶችን በመሸጥ 275 ሚሊየን ብር የተገኘ ሲሆን ÷ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ደግሞ 2 ነጥብ 68 ቢሊየን ብር መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
የገቢ አፈጻጸሙ 103 በመቶ መሆኑንና ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ88 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ማሳየቱን አመልክተዋል፡፡
የዲጂታል ክፍያ አማራጭ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ በአሁን ወቅት 95 ነጥብ 3 በመቶ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ገንብቶ ወደ ስራ በማስገባትና ስራ በማስጀመር 14 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡ 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: