የመጸዳጃ ቤት እና ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ የሚለቁ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እስከ 3 መቶ ሺህ ብር ድረስ እየተቀጡ መሆኑ ተነገረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከመኖሪያ ቤት የመጸዳጃ ቤት ወይም ማንኛውንም ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ወይም መስመሩን አገናኝተው ወንዙን የበከሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ከ150 ሺህ እስከ 3 መቶ ሺህ ብር እየቀጣ ይገኛል።
የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ወቅቱ የክረምት ወቅት በመሆኑ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ከግለሰቦች መኖሪያ እንዲሁም ከድርጅቶች የመጸዳጃ ቤት ወይም ማንኛውም ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ የሚለቁ እንዲሁም አካባቢን የሚበክሉ ግለሰቦች በባለስልጣኑ ደንቡ መሠረት እስከ 300 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይጣልባቸዋል።
ይህንን ህግ ጥሰው የተገኙ አካላት አሁን ላይ እየተቀጡ እንደሚገኙ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ አቶ የምስራች ጨምረው ገልፀዋል።
@Seledadotio

No comments yet.