የእግሊዝ አንጎል ፍልሰት

- Advertisement -
Sidebar AD

ወጣቶች አገራቸውን ጥለው ወደ አውስትራሊያ እየጎረፉ ነው።

#Ethiopia | ዘመናዊ ኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ እድገት በመምራት የምትታወቀው እንግሊዝ ወጣቱ ትውልዷ በታሪክ ታይቶ በማይታውቅ ደረጃ አገሩን ጥሎ ወደ ሌሎች አገራት ለመሰደድ መገደዱ ትልቅ መነጋገርያ ሆኗል።

በተለይም ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች አገራቸውን በመልቀቅ ወደ አውስትራሊያ የሚያደርጉት ፍልሰት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 አመት ብቻ ሀገራቸው ለቀው ወደ አውስትራሊያና ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተሰደዱ ወጣቶች ቁጥር ከ79,000 በላይ ይሆናል ተብሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት፣ የቤት ኪራይ እና የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ መናር እንዲሁም የግብር ጭማሪዎች ወጣቱን ትውልድ ክፉኛ ፈትነውታል።

በዚህም ወጣቶች በገዛ አገራቸው የተረጋጋ ሕይወት እና ተመጣጣኝ ገቢ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

ሀገራችን ለእኛ ለወጣቶች ምቹ ሀገር መሆን አቅቷታል እናም ህልማችንን እና ስኬታችንን ለማሳካት ግዴታ ውቅያኖስ መሻገር ነበረብን ሲሉ ተናግረዋል።

የወጣቱ ትውልድ ፍልሰት ለእንግሊዝ ኢኮኖሚ እና የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ትልቅ ስጋት መደቀኑ ነው የተነገረው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#England #economy #youth #migration #Australia #Sweden


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2