ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ አገኘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኮሜርሺያል ኖሚኒስ የሥራ አመራር ቦርድ የኮሜርሺያል ኖሚኒስን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ገምግሟል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከሚያቀርባቸው የአውትሶርሲንግ እና ሌሎች አገልግሎቶች ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማግኘት 805 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል፡፡

የ2018 በጀት ዓመት የገቢ እና ትርፍ እቅድ አፈጻጸም ከ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ14 ነጥብ 34 በመቶ የገቢ እና የ15 ነጥብ 4 በመቶ ያልተጣራ ትርፍ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት ከተያዘው የገቢ እና ትርፍ ዕቅድ አንጻር ኮሜርሺያል ኖሚኒስ 94 ነጥብ 8 በመቶ የገቢ እና 80 ነጥብ 4 በመቶ የትርፍ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡

የተመዘገበው አፈጻጸም አበረታች መሆኑን የገለጸው የሥራ አመራር ቦርዱ በቀጣይ የገቢ ስብጥርን በማስፋት፣ ወጪን በመቀነስ፣ እየቀረቡ ያሉ አገልግሎቶችን ጥራት በማሳደግ፣ ደንበኛ ተኮር አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ተጨማሪ ደንበኞችን በማፍራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በኮሜርሺያል ኖሚኒስ የሥራ አመራር ቦርድ የተገመገመ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡

ከ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ዕቅድ ጋር ሲነጻጸር የ53 ነጥብ 4 የገቢ እና የ56 በመቶ ያልተጣራ ትርፍ ጭማሪ ያለውን ይህን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም አመራር እና ሰራተኛ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት በዕቅድ ግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት ጥራት ያለው አገልግሎት በማቅረብ የደንበኞች እርካታን የማሳደግ እና ተጨማሪ ደንበኞችን የማፍራት እንዲሁም ገቢን ከማሳደግ አኳያ የታቀዱ አዳዲስ አገልግሎቶች እና ሌሎች የገቢ ምንጮች ትኩረት ተሰጥቷቸው ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡

የሥራ አመራር ቦርዱ በ2019 በጀት ዓመት የተያዙ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ግቦችን ለማሳካት የሚረዱ እቅዶች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲተገበሩ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: