የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ የዳኝነት አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግና ተቋማዊ ብቃትን ማሳደግ ላይ ተወያየ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን ማስጠበቅ፣ የፍርድ ቤቶችን አሰራር ማሻሻል እና የዳኝነት አገልግሎትን ለሕዝብ ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያየ።

ጉባኤውን የመሩት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፣ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን ከማስጠበቅ ባለፈ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ የዳኝነት አገልግሎትን ለተገልጋዮች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ፣ የሕዝብን እንግልትና አላስፈላጊ ወጪ ለመቀነስ የሚያስችሉ አሰራሮችን መዘርጋት እንደሚገባም አመልክተዋል።

በጉባኤው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤና የዳኝነት ግንኙነት መድረክ በአዋጅ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል።

በሰነዱ ውስጥ የተቋማዊ ብቃትን ለማሳደግ የሕጋዊ ውጤቶችን በግልጽ ማመላከት፣ ውሳኔዎችን ይፋ ማድረግ፣ የክትትል ሥርዓት መዘርጋት፣ የአፈጻጸም መለኪያዎችን ማዘጋጀት እና የሥልጣን ወሰኖችን በግልጽ መለየት የሚያስፈልጉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

የጉባኤው አባላትም በቀረበው ሰነድና በተነሱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ጉባኤውን አጠናቀዋል።

በጉባኤው ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፣ በአዋጁ አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የተጠቀሱት የጉባኤው አባላት ተገኝተዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1