#Ethiopia | የዓለማችን እውቅ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ አባት እና ወኪል የሆኑት ሆርሄ ሜሲ በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለያየታቸውን ኢንፎቤ ዘግቧል።
ላለፉት በርካታ ጊዜያት በጽኑ ህመም ሲታገሉ የቆዩት ሆርሄ ሜሲ በአርጀንቲናዋ ሮዛሪዮ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
የልጃቸውን የስፖርት ጉዞ ከመጀመሪያው አንስቶ በቅርበት ሲደግፉ የቆዩት አባቱ ሜሲ በሕፃንነቱ ወደ ባርሴሎና ሲያመራ አብረውት በመሄድና አዳዲስ ሁኔታዎችን እንዲላመድ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።
በሂደትም የሜሲ የስራ አስኪያጅ እና ዋና ተወካይ በመሆን ትልልቅ የሙያ ውሳኔዎችን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ምንም እንኳን ከሚዲያዎች ጋር ያላቸው ቅርበት የተገደበ ቢሆንም የሜሲ የስኬት ማማ ላይ መድረስ በስተጀርባ የነበሩ ዋና ሰው ነበሩ።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.